የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ጎበኙ

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ጎበኙየትራንስፖርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ አዲስ የተሾሙት የተከበሩ አቶ አህመድ ሺዲ ህዳር 21/2009 ዓ.ም በአቪዬሽን ሴክተር ተቋማት ተገኝተው የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝታቸውም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ጋር ወይይት አድርገዋል፡፡

በዕለቱም የኢትጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው ባለስለጣን መስሪያ ቤቱ የተቋቋመበትን ዋና ዓላማ፣ መስሪያ ቤቱ በእስካሁኑ ጉዞው ያከናወናቸው ተግባራት፣ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ሴክተር ተቋም ያለችበትን ደረጃ የሚያሣይና በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአለበትን ሃላፊነት፣ እየተሠሩ ያሉ ተግባራትና ወደፊት ሊሠሩ የታሰቡ ፕሮጀክቶችንና እንደተቋም የሚታዩ ችግሮችን ለክቡር ሚንስትሩ በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ሚንስትሩ እና የማኔጅመንት አባላት ውይይት አድርገዋል፡፡

በእለቱም ሚንስትሩ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘውን የአቪዬሽን ባለሙያዎች  ስልጠና ማእከልን፣ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የሚገኘውን ታወር፣የኮሙዩኒኬሽንና ናቪጌሽን እንዲሁም  የአየር ትራፊክ መቆጣሪያ መሳሪዎችን ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስተሩ ሃገራችን ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ የደረሰችበትን ደረጃ በማድነቅ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ሚንስትር መስሪያ ቤቱ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ  ክቡር ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡